Tuesday, August 12, 2014

አዲስ ጉዳይም እንደ አዲስ ነገር

በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በአመፅ ለመናድ በማሴር ጠርጥሬ ከሰስኳቸው ካላቸው  የህትመት ውጤት አሳታሚዎችና ድርጅቶች መካከል የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ባልደረቦች ሃገር ጥለው መሰደዳቸው ተነገረ። በማህበራዊ ድረ-ገጾች የተጻፉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የመጽሔቱዋን ባለቤት እንዳልካቸው ተስፋዬን ጨምሮ የመጽሔቱዋ ምክትል ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ፣ ከፍተኛ አጋዘጅ ጋዜጠኛ እንዳለ ተሽ እና አዘጋጅና አምደኛ ሀብታሙ ስዩም ሀገር ጥለው ለመሰደድ ተገደዋል።
ሐምሌ 26/2006 የፍትህ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ፋክት፣ ጃኖ፣ ሎሚ፣ አዲስ ጉዳይ እና እንቁ የሚባሉ መፅሄቶችና አፍሮ ታይምስ የሚባል ጋዜጣ አሳታሚዎችና ድርጅቶችን በየጊዜው ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ የአመፅ ቅስቀሳና የሀሰት ወሬዎችን በመንዛት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ በሀይል እንዲፈረስ  እና ህዝብ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርጉ የወንጀል ተግባራትን በመፈፀም  በሚል ጠርጥሮ መክሰሱን ማስታወቁ አይዘነጋም።

No comments:

Post a Comment