Tuesday, April 8, 2014

ሰበር ዜና፡- ወ/ሮ አስቴር ማሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ተሾሙ



በቅርብ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት በተመረጡት አቶ ሙክታር ከድር ምትክ፣ ወ/ሮ አስቴር ማሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪ ሆነው ተሾሙ፡፡

ማክሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. በፓርላማ ሹመቱ የፀደቀላቸው ወ/ሮ አስቴር በተጨማሪ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አቅራቢነት በፓርላማው ሹመታቸው የፀደቀው ወ/ሮ አስቴር የመጀመርያዋ ከፍተኛ ተሿሚ ናቸው፡፡


‹‹ሴት ተሿሚ ለዚህ ከፍተኛ ሹመት በማቅረቤ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል፤›› ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማው አባላት ስሜታቸውን ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ አስቴር ሹመታቸው ከፀደቀ በኋላ ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡

በተለያዩ ከፍተኛ የፓርቲና የመንግሥት ኃላፊነቶች ላይ የቆዩት ወ/ሮ አስቴር፣ በፓርላማው የመንግሥት ተጠሪና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሆነው ሠርተዋል፡፡
http://www.ethiopianreporter.com

No comments:

Post a Comment