Thursday, September 19, 2013

ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 9 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2005 የትምህርት ዘመን የ12  ክፍል  የመሰናዶ  ፈተናን  ካለፉት 163ሺህ 406  ተማሪዎች መካከል  103 ሺህ 394 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዋል ።

ምደባው ዛሬ  በአገር አቀፍ የትምህርት ምዘና  ኤጀንሲ  የተማሪዎቹ  የዩኒቨርሲቲ  ድልደላ  ተካሂዷል ።

ተማሪዎችም የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ  በኤጀንሲው ድረ ገፅ http://www.nae.gov.et/ በመግባት placement result የሚለውን  በመጫን መመልከት ይችላሉ ።

ወይም በአጭር የፅሁፍ መልዕክት plr ፅፎ  የመለያ  ቁጥርን በማስከተል ለ8181 በመላክ የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ  ማወቅ  የችላሉ ብሏል ኤጀንሲው ።



ምደባው የተከናወነው የ70/30 ቀመርን ባሟላ  መልኩ ከጠቅላላ  ተፈታኞች  ደግሞ  40  በመቶዎቹ  በምህንድስና  ሳይንስ ዘርፍ እንዲገቡ ተደርጓል ።

በምደባው የሴቶችን ተሳትፍ  38 በመቶ  እንዲሆን ታሳቢ  ተደርጎ የተከናወነ ሲሆን ፥ የህክምና  ሳይንስን ምርጫቸው ያደረጉ  ተማሪዎች ደግሞ የመቁረጫ  ነጥብን  ለወንዶች 482  ለሴቶች ደግሞ 477 እንዲሆን  ተደርጓል ።

የምደባ  መመሪያው  በሚፈቅደው መሰረትም  የከፍተኛ  ትምህርት ተቋማትን የቅበላ  አቅምን ታሳቢ ተደርጎ ሴት ተማሩዎች ከወንዶች ጋር ተወዳድረው ከሚያገኙት በተጨማሪ 3 በመቶ እርስ በርሳቸው  ተወዳድረው ወደሚፈልጉት የትምህርት መስክ እንዲገቡ መደረጉን ነው  ኤጀንሲው የገለፀው ።

የሚያጠቡ እናቶች በአቅራቢያቸውና   ተመሳሳይ  ፆታ  ያላቸው  መንትያዎች በአንድ ቦታ እንዲመደቡ እንዲሁም ፥  የጤና  ችግር ያለባቸው  ባቀረቡት  ማስረጃ  መሰረት  ምላሽ  እንዲያገኙ  ተደርጓል ።

በዘንድሮው ድልደላ  በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሴቶች  ቁጥር ተመጣጣኝ  እንዲሆን  ተደርጓል ።

በኮምፒውተር ታግዞ የተከናወነው ምደባ  የተማሪዎችን ውጤት ፣ የትምህርት መስክንና  የዩኒቨርሲቲ ምርጫን መሰረት በማድረግ  በውድድር ብቻ ተከናውኗል  ብሏል ኤጀንሲው ።

መቀሌ  ዩኒቨርሲቲ  7 ሺህ 312  ተማሪዎቸን  በመቀበል  ቀዳሚው  ሲሆን ፥ አዳማ   ዩኒቨርሲቲ 5 ሺህ 134  ተማሪዎች በመቀበል በሁለተኝነት ሲቀመጥ ፥  4 ሺህ 495 ተማሪዎችን የተቀበለው ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ  ሶስተኛ  ነው ።

ዝቅተኛ  ቁጥር  ያለው ተማሪ  የተቀበለው  ኮተቤ  መምህራን  ትምህርት  ኮሌጅ 955  ተማሪዎች  ተመድበውለታል ።
http://www.fanabc.com

No comments:

Post a Comment