Friday, August 9, 2013

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ነገ በሁለት ፍጻሜዎች ይጠበቃሉ



ነገ ረፋድ 5 ሰአት 20 ላይ የወንዶች 800 ሜትረ ማጣሪያ መሃመድ አማን እና አማን ወጤ ሃገራቸውን ይወክላሉ።
ቀትር 8 ሰአት ላይ ደግሞ በሴቶች ማራቶን ቲኪ ገላና አበሩ ከበደ ፈይሴ ታደሰ መሰረት ሃይሉና  መሰለች መልካሙ በሞስኮው ጎዳናዎች ኢትዮጵያን ወክለው 42 ኪሎ ሜትሩን ይሮጣሉ።
ማምሻውን 11 ሰአት 20 ላይ ደግሞ ሶፊያ አሰፋ ህይዎት አያሌው እቴነሽ ዲሮ 3 ሺህ መሰናክል ሴቶች ይወዳደራሉ።
ኢትዮጵያውያን የበላይ የሆኑበት እና ለወርቅ ሜዳልያ የሚጠበቁበት 10 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍጻሜም 12 ሰአት 55 ሲካሄድ ደጀን ገብረመስቀል አበራ ኩማ ኢማነ መርጊያና ኢብራሂም ጀላን የበላይነታቸውን ለማስጠበቅ ይሮጣሉ።

No comments:

Post a Comment