Friday, August 30, 2013

የዩኒቨርሲቲና የመሰናዶ መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 24 ፣ 2005 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና መሰናዶ መግቢያ ውጤትን ዛሬ ይፋ አደረገ።
የዩኒቨርሲቲ መግቢያና ወደ መሰናዶ ማለፊያ ነጥብን ለመወሰን ፥ የዩኒቨርስቲዎችን ቀጣይ የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ሳሙኤል እንዳሉት ፥ ዘንድሮ ወደ ዩኒቨርሲቲ የገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከአምናው የ95 554 ብልጫ አሳይቷል። በዚህም መሰረት 10ኛ ክፍል ተፈትነው ወደ መሰናዶ ለመግባት ፥ ለወንዶች 2.71 እና ከዛ በላይ ለሴቶች 2.29 እና ከዛ በላይ ። ለሁሉም ክልሎች ማየትና መስማት ለተሳናቸው ፥ 2.14 እና ከዛ በላይ ፤ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ለወንድ 2.29 እና ከዛ በላይ ፣ ለሴት 2.14። ለግል ተፈታኞች ፤ ለወንድ 2.86 እና ከዛ በላይ ፣ ለሴት 2.29 እና ከዛ በላይ ሆኖ ተወስኗል። 12ኛ ክፍል ተፈትነው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት 265 መቁረጫ ነጥብ ሆኖ ተወስኗል።


ወደ ዩኒቨርሲቲዎች መግቢያ ነጥብም ፥ በተፈጥሮ ሳይንስ ፤ ወንድ 325 እና ከዛ በላይ እንዲሁም ለሴት 305 እና ከዛ በላይ። ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ወንድ 305 እና ከዛ በላይ ሴት 300 እና ከዛ በላይ መግቢያ ነጥብ ሆኗል። ለግል ተፈታኞች ወንድ 330 እና ከዛ በላይ ሴት 320 እና ከዛ በላይ መግቢያ ነጥብ ይሆናል። በማህበራዊ ሳይንስ ወንድ 285 እና ከዛ በላይ ሴት 280 ከዛ በላይ ሲሆን ፥ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ፤ ወንድ 275 እና ከዛ በላይ ሴት 270 እና ከዛ በላይ መግቢያ ነጥብ ሆኖ ተወስኗል።

 መስማት ለተሳናቸው 270 እና ከዛ በላይ ሲሆን ፥ ማየት ለተሳናቸው ደግሞ 230 እና ከዛ በላይ መግቢያ ነጥብ ይሆናል። ለሁሉም የግል ተፈታኞች ደግሞ 290 እና ከዛ በላይ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ሆኖ ተወስኗል። በዚህም መሰረት 265 መቁረጫ ነጥብ ያመጡ ተፈታኞች በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የማታ እንዲሁም፤ በግል ኮሌጆች እና ከፍትኛ የትምህርት ተቋማት በቀን መርሃ ግብር ትምህርታቸውን መከታተል ይችላሉ።

 መንግስት እየተገበረ ያለው 70% በተፈጥሮ ሳይንስና እና 30% ማህበራዊ ሳይንስ እንደተበቀ ሆኖ ፥ በተፈጥሮ ሳይንስ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከገቡ ተማሪዎች መካከል 40.2% በኢንጅነሪንግ ትምህርት እንደሚመደቡም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምደባም በቅርቡ ይፋ ይሆናል።
(ኤፍ.ቢ.ሲ) 

No comments:

Post a Comment