Sunday, August 18, 2013

አርቲስት እዮብ መኮንን ከዚህ አለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት እዮብ መኮንን ከዚህ አለም በሞት ተለየ። አርቲስት እዮብ ባለፈው ማክሰኞ ማለዳ ላይ በድንገተኛ አደጋ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል መግባቱ ይታወሳል። ድምፃዊው በዕለቱ በብስክሌት ሰውነቱን አፍታቶ ወደቤቱ ሲመለስ በመውደቁ ምክንያት ሆስፒታል ገብቶ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቷል። አርቲስት እዮብ የተሻለ ህክምና ለማግኘት ወደ ኬንያ በመሄድ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ሌሊቱን ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለአድናቂዎቹ እና ለመላው ቤተሰቡ መጽናናትን ይመኛል።
http://www.fanabc.com

No comments:

Post a Comment