Monday, July 22, 2013

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፊፋ ጥያቄ አቀረበ

ብራዚል ለከርሞ በምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ተካፋይ ለመሆን እየተደረገ ባለው ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምድቡን በ10 ነጥብ ይመራል፡፡ ከማዕከላዊ አፍሪካ ጋር አንድ የመጨረሻና ወሳኝ ጨዋታ ከሜዳው ውጪ ይጠብቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡድን ከማዕከላዊ አፍሪካ ጋር ከሜዳው ውጪ አንድ ጨዋታ እየቀረው ወደ ቀጣዩ አንድ የደርሶ መልስ ጨዋታ ማለፉን ባረጋገጠ ማግስት፣ ፊፋ የኢትዮጵያ ቡድን ቦትስዋናን ገጥሞ ያሸነፈው ‹‹ተገቢ ያልሆነ ተጫዋች አሰልፎ ነው›› በሚል በደረሰው መረጃ መሠረት ሦስት ነጥብና ሦስት ጐል ከኢትዮጵያ ቡድን ላይ እንዲቀነስ መወሰኑም ይታወሳል፡፡

በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ ቡድን ለመርሐ ግብር ማሟያ ከማዕከላዊ አፍሪካ ጋር ከሜዳው ውጪ ሊያደርግ የነበረው ጨዋታ፣ የምር ሆኖ እንዲጠበቅም ግድ ብሏል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማዕከላዊ አፍሪካ ውስጥ ያለውን የፀጥታ ችግር በመጥቀስ፣ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የሚደረግበትን ገለልተኛ ሜዳ እንዲያሳውቀው ጠይቋል፡፡

በሌላ በኩል ዜናው ከተረጋገጡ ምንጮች ባይገለፅም፣ የኢትዮጵያ ተጋጣሚ ማዕከላዊ አፍሪካ የፀጥታ ችግር እንደሌለበትና ጨዋታውንም አገሯ ላይ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች መሆኑዋን የሚናገሩ አሉ፡፡
http://www.ethiopianreporter.com

No comments:

Post a Comment