Wednesday, February 27, 2013

Masresha Bekele (Professor) Remembers Yoftahe,Yohannes and Yonas


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ማስረሻ በቀለ እነ ዮሃንስ አድማሱ እና ዮናስ አድማሱን ያፈራው ትውልድ አባል ናቸው፡፡በተለይም ኢትዮጵያዊ መፃህፍትን አጥብቀው የሚሹ የዚህ ትውልድ አባላት ጠንቅቀው ያውቋቸዋል፡፡አሁን ያሉበት የዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ በገበያው ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙ መፃህፍትን ለህትመት በማብቃት ላይ ነው፡፡በዮሃንስ አድማሱ ጥረትና ድካም ተዘጋጅቶ በታናሽ ወንድሙ ዮናስ አድማሱ(ዶ/ር) የህትመት ብርሃን ያየው “ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ-አጭር የህይወቱና የፅሁፉ ታሪክ" የተሰኘ መፅሃፍ የምረቃ ፕሮግራም ላይ ይህንን ንግግር አድርገው ነበር፡፡በንግግራቸው የመፅሃፉን የህትመት ሂደት እና ከወንድማማቾቹ ጋር የነበራቸውን ምሁራዊ ወዳጅነት አጠር አጠር አድርገው ለታዳምያኑ አካፍለዋል፡፡የመተረክ ችሎታቸውና ለዛቸው ልዩ ነው፡፡በሸገርTribune ሊያደምጡት ይችላሉ፡፡

No comments:

Post a Comment