Saturday, December 10, 2011

የወረደው የ"TK" እና ሊያ ከበደ ወረድ ወረድ



ሙዚቃውን የተጫወተው "TK" ቤተሰቦቹ ሙዚቀኛ ቢሆኑም በኢትዮጵያ ስሙ አይታወቅም፡፡አሁን ነዋሪነቱ በአሜሪካን ሃገር ነው፡፡ሰሞኑን የተለቀቀው ይህ "ቦሌ ቦሌ"የተሰኘ ሙዚቃ ዳይሬክት የተደረገው በሊያ ከበደ ሲሆን ሜሮን ክብረት ፕሮዲውስ አድርጋዋለች፡፡የረባ ግጥምም ሆነ ማራኪ ዳንስ አይታይበትም፡፡በተለይ ሚዚቃው ካለ ቪዲዮው ምንም ትርጉም አይሰጥም፡፡ምናልባት እኔ በሙዚቃ ከቪዲዮ ይልቅ ዜማን ስለማስቀድም ይሆናል፡፡ሙዚቃው በሚገኝባቸው ድረ ገፆች በርቱ እና እፈሩ የሚሉ አስተያየቶችን ተመለክቼ እኔ እፈሩ ወደሚለው አደላሁ፡፡ሌሎች ስለሙዚቃው የሆነ ነገር ቢሉ ብዬ ነው እዚህ share ያደረኩት፡፡እነ ሊያ በዚህ ስራቸው ወይ የኢትዮጵያውን አሊያም የሚኖሩበትን የአሜሪካን የሙዚቃ ባህል ማሳየት የቻሉ አልመሰለኝም፡፡ወረድ ወረድ..ወረድ ብቻ ብለዋል፡፡ምናልባት ሙዚቃውን የወደዱት ካሉ የሊያ ከበደ ዝና ብቻ እንዳልገዛቸው አስባለሁ፡፡
ለማንኛውም የወረደው ወረድ ወረድ ይኸውላችሁ፡፡


No comments:

Post a Comment