Saturday, December 17, 2011

ተማሪው በሁለት ተማሪዎች በጩቤ ተወግቶ ተገደለ


                
መስቀል ፍላወር አካባቢ በሚገኘው አደይ አበባ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ /ቤት፣ 12 ክፍል ተማሪ የነበረው 18 አመቱ ወጣት ፍቅረዮሐንስ ብርሃኑ፤ በሁለት 9 ክፍል ተማሪዎች በጩቤ ተወግቶ ተገደለ፡፡ በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የብሔር ብሔረሰቦች በአል ሲከበር ተማሪ ፍቅረዮሐንስ በሞባይሉ ዝግጅቱን በመቅረፅ ላይ ሳለ ከኋላ የነበሩት ተማሪ አቤል መንገሻ እና  ቢኒያም ግደይከለልከንበሚል በአንኳር አፈር ጀርባውን እንደመቱት የገለፁልን የሟች ቤተሰቦች፤ መልስ ሳይሰጥ ወደ ቤቱ በሚሄድበት ወቅትዝምታህ ንቀት ነው ሰኞ እንገናኝበማለት እንደዛቱበትም ይናገራሉ፡፡ ሰኞ /ቤት አርፍዶ በመድረሱና የት/ቤቱ በር በመዘጋቱ ወደ ቤቱ የተመለሰው ፍቅረዮሐንስ፤ ቀኑን ሙሉ ሲያጠና መዋሉን ቤተሰቦቹ ገልፀዋል፡፡

ማክሰኞ በትምህርት ገበታው ላይ የተገኘው ፍቅረዮሐንስ፤ የጠዋቱን የትምህርት /ጊዜ አጠናቆ ምሳውን ከበላ በኋላ ወደ ክፍሉ ሲያመራ ተማሪ አቤል መንገሻ እና ተማሪ ቢኒያም ግደይ ያገኙትና በያዙት ጩቤ ጀርባው ላይ ሁለት ጊዜ አከታትለው ይወጉታል፡፡ ወጣቱ ከአፍና ከአፍንጫው ደም ይፈሰውና ይወድቃል፡፡ በሁኔታው የተደናገጡ ተማሪዎች ፍቅረዮሐንስን ወደ ሰናይ የህክምና ማዕከል የወሰዱት ሲሆን ህክምና ከማግኘቱ በፊት ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል፡፡ ለወላጆቹ የመጀመሪያ ልጅ የነበረው ሟች፤ ጥሩ ውጤት ለማምጣት ሌሊቱን ሙሉ ሲያጠና ያድር እንደነበር የተናገሩት ቤተሰቦቹ፤ /ቤቱ ከሌላ /ቤት የተባረሩ ስነምግባር የሌላቸውን ልጆች በመቀበሉ ነው ድርጊቱ የተፈፀመው ብለዋል፡፡ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የት/ቤቱ መምህር በበኩላቸው፤ ሁለቱ ተማሪዎች ዘንድሮ ወደ /ቤቱ የመጡ ቢሆንም ውጤታቸው ጥሩ እና ፀባያቸውም መልካም እንደሆነ ከካርዳቸው ላይ አረጋግጠን ነው የተቀበልናቸው ይላሉ፡፡ /ቤቱ እንደዚህ አይነት ችግር ገጥሞት እንደማያውቅና ተማሪዎቹ በፍቅርና በመተሳሰብ የቆዩ መሆናቸውን የገለፁት መምህሩ፤ ስለታማ ነገር ወደ /ቤቱ ይዘው መግባታቸውን ለመቆጣጠር እንደማይቻልና በምሳ ዕቃቸውም ቢሆን ደብቀው ሊገቡ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ ድርጊቱን ፈጽመዋል ብሎ የጠረጠራቸውን ሁለቱን ተማሪዎች በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ ታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment