Saturday, August 20, 2011


የሌላ አለም ፍጡራን እጆች በላሊበላ?
ከ11ኛው እስከ 13ኛው መ.ክ.ዘ. የታነፁት የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ለኢትዮጵያ ቀደምት ስልጣኔ ምስክር ናቸው፡፡ምንም እንኳ አውሮፓውያኑ በዚያን ዘመን ኢትዮጵያውን ላሊበላን ማነፅ የሚያስችል የስልጣኔ ደረጃ እና ኪነ ህንፃ ነበራቸው ብለው ለማመን ቢቸገሩም፡፡የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕምናን ከሃገሪቱ የስልጣኔ ምስክርነት ባሻገር መንፈሳዊ ትርጓሜም አላቸው፡፡ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የታነፁበት ዘመን፤ኪነ ህንፃ እና የኪነ ህንፃው ባለቤትነት ለዘመናት ሲያከራክሩ የቆዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡

እንግሊዛዊው ጋዜጠኛ እና ፀሃፊ ግርሃም ሃንኩክ ስለ አብያተ ክርስቲያናቱ የግንባታ ሂደት የተለየ አቋም አላቸው፡፡እንደ ግርሃም ሃንኩክ እምነት የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የኢትዮጵያውያን ስልጣኔ ውጤት ነው፡፡በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ዘጋቢ ፊልሞችን በመስራት የሚታወቀው ሂስተሪ ቻናል( History.com) Ancient Aliens and Lalibela churches in Ethiopia በሚል ርዕስ አንድ ዘጋቢ ፊልም ሰርቷል፡፡



የቴሌቭዥን ጣቢያው በዘጋቢ ፊልሙ የላሊበላ ኪነ ህንፃ የኢትዮጵያውያን ብቻ አይደለም፤በላሊበላ ኪነ ህንፃ ግንባታ የሌላ አለም ፍጡራን( Aliens) እጅ አለበት ይላል፡፡የዘጋቢ ፊልሙ አዘጋጆች በስራቸው የታሪክ ፀሃፊዎች፤ተመራማሪዎች የሌላ አለም ፍጡራን (Aliens) እና ያልታወቁ በራሪ አካላት(UFO) አጥኚዎችን ግምቶች እንዲሁም በመፅሃፍ ቅዱስ ታሪኮች እና አፈታሪኮች ላይ ተመርኩዘው የሚሰጧቸውን ትንታኔዎች አካተዋል፡፡



No comments:

Post a Comment