Sunday, July 31, 2011



(ሪፖርተር)

SUNDAY, 31 JULY 2011 00:00
BY HENOCK YARED
በፋሺስት ኢጣሊያ 75 ዓመት በፊት ሰማዕት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ የተቀበሩበት ቦታ በአዲስ አበባ በስተደቡብ በለቡ አካባቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አስታወቀች፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፉሪ ምስካበ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖትና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አባ ሳሙኤል ተክለ ማርያም ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት ከሆኑ በኋላ የተቀበሩት ፋሺስቶች በመኖርያነትና በእስር ቤትነት ይጠቀሙበት በነበረውሙኒሳ ጉብታላይ ነው፡፡

የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል በሐምሌ 22 ቀን 1982 .. ሰማዕቱን ገድሎ አስክሬናቸው አደባባይ ላይ ጥሎ ከዋለ በኋላ፣ ቀብራቸው በምስጢር መፈጸሙ መዛግብት እንደሚያስረዱ ያስታወሰችው ቤተ ክርስቲያኗ፣ የእኚህን ታላቅ አባት ቀብር በምስጢር የተፈጸመበት ቦታ ለማግኘት የተለያዩ ምሁራን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ የታሪክ ሰነዶችን ሲመረምሩ ቢቆዩም፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስከአዲስ አበባ በስተደቡብ በምስጢር ቀበሯቸውከሚል ጠቅላላ ፍንጭ ያለፈ ምንም ዓይነት የተረጋገጠ ማስረጃ ሳይገኝ ቆይቶ ነበር ብላለች፡፡ 

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ከአዲስ አበባ ከተማ መስፋፋት ጋር ተያይዞለቡተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሰፈሩ ምዕመናን በአካባቢው ተወልደው ካደጉ አረጋውያን ጋር ባደረጉት ማኅበራዊ ግንኙነት ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፋሽስቶች በመኖርያነትና በእስር ቤትነት ይጠቀሙበት በነበረውሙኒሳ ጉብታላይ መቀበራቸውን ከወላጆቻቸው ሲሰሙ እንዳደጉ በእርግጠኝነት አስረድተዋቸዋል፡፡ 

የኢጣሊያ ፋሺስት 1928 .. በኢትዮጵያ ላይ የግፍ ጦርነትን ባነሣ ጊዜ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ከጦር ሥፍራ ለመለየት ስላልሆነላቸው፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ተከትለው ወደ ሰሜን ጦር ግንባር ዘምተዋል፡፡ ፋሺስቱ በማይጨው የመርዝ ጦርነት ከማድረጉ የተነሣ፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሲበታተንም ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር የተመለሱት አቡነ ጴጥሮስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሔደው ለአገርና ለነፃነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን ለሰላሌ አርበኞች በመስበክም ይታወቃሉ፡፡ 

አርበኞች አዲስ አበባን በሁለት አቅጣጫዎች ከሰሜናዊ ምዕራብ (ባሕር) እና በደቡባዊ ምሥራቅ (ሊባ) አቅጣጫ ለመቆጣጠር ውጊያ በከፈቱበት ጊዜ የተማረኩት አቡነ ጴጥሮስ፣ ለፋሺስት እንዲገዙ፣ የኢጣሊያ መንግሥት ገዢነትንም አምነው አሜን ብለው እንዲቀበሉ ግፊት ቢያደርጉባቸውም፤ እምቢኝ ለአገሬና ለሃይማኖቴ ብለው ለሰማዕትነት ያበቃቸውን የሞት ጽዋ መቀበላቸው በታሪክ ተመዝግቧል፡፡
ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የራሷን  ጳጳሶች 1921 .. በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ ጊዜ ስትሾም አንዱ አቡነ ጴጥሮስ ነበሩ፡፡
በተያያዘ ዜናም አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት የተቀበሉበትን 75 ዓመት ለማሰብም ቅዳሜ ሐምሌ 23 ቀን 2003 .. 8 ሰዓት ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ዐውደ ጥናት መካሔዱንና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁራን በሰማዕቱ ää ዙርያ አራት ጥናቶችን ያቀረቡ መሆናቸው ታውቋል፡፡ 
1875 .. የተወለዱት አቡነ ጴጥሮስ፣ää ዘምሥራቀ ኢትዮጵያተብለው፣ራሱ በሽሎ መለስ፣ እግሩ አቦክ ፈረንሳዊ ወሰን ድረስ (ጅቡቲ)” 21 አካባቢዎችን ያስተዳድሩ ነበር፡፡

No comments:

Post a Comment